Page 9 - עלון מידע לצרכן - אמהרית
P. 9

የአደጋ ጊዜ የውሃ ኣጠቃቀም - ለእርስዎ ተዘጋጅቷል!

በኣለማችን ከስድስት ሰዎች ኣንዱ መጠጥ ውሃ የማግኘት ዕድሉ የለውም!

የውኃ አቅርቦቱ ቀላል ጉዳይ አይደለም፣ እንደ እነ ብክለት፣ አውዳሚ የመሬት መንቀጥቀጦች፣ ጦርነቶች እና እንዲሁም ያልታቀደ የውሃ መቆራረጥ ላሉት ያልተጠበቁ ክስተቶች ተጋላጭ ነው።
እኛ ሜይ ሼቫ’ዎች ከላይ በተገለጹት በእያንዳንዱ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን በቢር ሼቫ እና ኦፋኪም ከተሞች በስፋት በተሰራጩ የውሃ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኣማካኝነት ውሃ ለማቅረብ በተመቻቸ ሁኔታ ተዘጋጅተናል።
ሆኖም ነገሮችን ለማደራጀት ጊዜ ይወስዳል። ስለሆነም በዚህ ጊዜ የውሃ አቅርቦት አይኖርም።
የእርስዎን የመቋቋም ሂደት ቀላል ለማድረግ እያንዳንዱ ቤተሰብ በቀን 4 ሊትር ውሃ ለአንድ ሰው አስቀድሞ እንዲያዘጋጅ ይመከራል። በHome Front Command መመሪያ መሰረት ይህ ለ3 ቀናት መዘጋጀት አለበት። እንደየ
ኣስፈላጊነቱ ደግሞ - የአጠቃቀም ገደብ እና ጥንቃቄ ላይም ትኩረት ያድርጉ።
ውሃ ንፅህናን ለመጠበቅም እንጠቀማለን፣ በድንገተኛ የውሃ መጥፋት ጊዜ ንፅህናን ለመጠበቅ የሚረዳ የንፅህና መጠበቂያ ኪት መዘጋጀት አለበት።

እርጥብ መጥረጊያዎች ወይም የፀረ-ባክቴሪያ ጄል እሽግ -
በውሃ ምትክ የግል ንፅህናን ለመጠበቅ የሚረዱ
የሚጣሉ የመመገቢያ ሰሃኖች እና ሶፍት
የቆሻሻ ማጠራቀምያዎች
ለንፅህና ፍላጎቶች የንፅህና ቦርሳ - በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ጥቅም ላይ
የሚውሉ ልዩ ቦርሳዎች

በአደጋ ጊዜ፣ ከማዘጋጃ ቤቱ የስልክ መስመር ፊት ለፊት ያሉት መመሪያዎች ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር መቀየር አለባቸው። 1-800-303-707 (106)

   ለበለጠ መረጃ የኮርፖሬሽኑን ድረ-ገጽ ይጎብኙ፡ www.mey7.co.il                                              9
በተጨማሪም የHome Front Command ድህረ ገጽ፡ www.oref.org.il ላይ
   4   5   6   7   8   9   10   11   12